የጥበቃ አገልግሎት ለመስጠት የጨረታ ማስታወቂያ
Tender Notice for Security Service Provision
የረጲ ቁጥር አንድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር ለአንድ ዓመት የጥበቃ አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሆኑ ድርጅቶችን በጨረታ መፈለግ ይፈልጋል።
የረጲ ቁጥር አንድ (1) የጋራ መኖሪያ ባለቤቶች ሀ/የተ/ህ/ስ/ማህበር የጥበቃ አገልግሎት የመስጠት ሥራ ላይ የተሰማሩና በዚህ የሥራ ዘርፍ በቂ ልምድ ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በማህበራችን ፍላጎት መሰረት በአካል ብቃታቸውም ሆነ በዘርፉ በሚመለከታቸው አካል የተመዘገበና የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በተጨማሪም በቂ ስልጠና ያላቸውን ሠራተኞች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ለአንድ ዓመት የኮንትራት ውል (እንደ አስፈላጊነቱ የሚታደስ) ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ከማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርበታል። ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ ረጲ ቁጥር አንድ የጋራ መኖሪያቤቶች ህ/ስ/ማህበር ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
Repi 1 Condominium Owners Association intends to select, through competition, legal companies that are engaged in security service provision with sufficient experience in this field, registered and renewed by relevant authorities, having paid current taxes and holding a tax identification number, and able to provide adequately trained staff, for a one-year contract (renewable as necessary). Bidders are required to obtain the tender document from the Association office upon payment of a non-refundable fee of 300.00 Birr. A bid security must be provided in the form of a bank-confirmed CPO. The Association reserves the right to cancel the tender partially or entirely. The tender document can be purchased within ten (10) working days from the date of publication in the Reporter newspaper, by appearing at the Repi 1 Condominium Association office during working hours.
- 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 300.00 ETB
- ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: የጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ ልምድ ያላቸው፣ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የሰለጠኑ ሰራተኞች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.