BinaSmart ዜና 💼 Own a company?
አቅርቦት Supply

የአብሪ ሳጥን (Light Box) ማስታወቂያ ሰሌዳ አሰርቶ ለማስገጠም የወጣ ግዢ ጨረታ

Tender for the Fabrication and Installation of Light Box Signage

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ.·📍 Ethiopia
🗓 Deadline: 24 Sept 2026

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል ለሚገኙ 23 ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዎች የአብሪ ሳጥን (light box) ማስታወቂያ አሰርቶ ቦታው ድረስ ወስዶ በመግጠም ለማሰራት ብቁ የሆኑ የማስታወቂያ ድርጅቶችን ይፈልጋል።

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል ለሚገኙ 23 ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዎች የሚሆን የአብሪ ሳጥን (light box) ማስታወቂያ አሰርቶ እና ቦታው ድረስ ወስዶ በመግጠም በሙያው ልምድና ብቃት ያለውን የማስታወቂያ ድርጅት አወዳድሮ በውል (ኮንትራት) መፈራረም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቲን ሰርተፍኬት፣ እሴት ታክስ ምዝገባ እና የሙያ ፍቃድ እንዲሁም አገልግሎቱን የማቅረብ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው። የጨረታ ሰነድ ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከኩባንያው ዋና መ/ቤት ገንዘብ ቤት ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይቻላል። የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) በሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ስም መሆን አለበት። የተሟላ የመጫረቻ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያ እና ደጋፊ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኩባንያው ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ኩባንያው ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

English
Hibret Insurance S.C. invites qualified advertising companies to participate in a tender for the fabrication, delivery, and installation of light box signage for its 23 branches and liaison offices across the country. Bidders must have a renewed business license, TIN certificate, VAT registration, professional license, and relevant experience. Tender documents can be purchased from the company's head office cashier starting from Pagume 3, 2018 E.C. upon payment of a non-refundable fee of ETB 200.00. A bid bond of ETB 50,000.00 in the form of a bank guaranteed check (CPO) in favor of Hibret Insurance S.C. must be submitted with the bid. Sealed bids, including price and technical/financial documents, must be deposited in the tender box at the 9th floor of the head office by Meskerem 14, 2019 E.C. at 8:00 AM. Bids will be opened on the same day at 9:00 AM at the meeting hall on the 11th floor. The company reserves the right to cancel the tender partially or entirely.
ዝርዝሮች · Details
  • 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: ብር 50,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.)
  • 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: ብር 200.00
  • 📥 ማስረከቢያ · Submit to: የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 9ኛ ፎቅ የጨረታ ሳጥን
  • 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-24
  • ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቲን ሰርተፍኬት፣ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የሙያ ፍቃድ እና አገልግሎቱን የማቅረብ ልምድ
አድራሻ · Contact
🏢 ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ.
📞 +251 11 1 26 34 34 (የውስጥ መስመር 160/402/190)
📍 ቴዎድሮስ አደባባይ አከባቢ፣ የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ

ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)

🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ

Get tenders like this the moment they publish.

Subscribe →