BinaSmart ዜና 💼 Own a company?
ሽያጭ ጨረታ Disposal auction

ሕብረት ባንክ አ.ማ. የሕብር ሕንፃ 9ኛ ወለል ለቢሮ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማከራየት

Hibret Bank Vacancy: Lease of 9th Floor of Hibir Building for Office Use via Open Bid

Hibret Bank S.C.·📍 Ethiopia
🗓 Deadline: 2 Oct 2026

ስለ ጨረታው · About this tender

ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የሕብር ሕንፃ 9ኛ ወለል ለቢሮ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል። ኪራይ ፈላጊዎች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ ይችላሉ።

ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብር ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። ጨረታ ቁጥር፡ ሕባ/001/2019። ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ማለትም ከመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በመገኘት መግዛት ይቻላል። ለጨረታ የቀረበውን ወለል ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከመስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፣ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለጨረታ የቀረበውን ይዞታ ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የዋስትናው የአገልግሎት ጊዜውም /Validity Date/ ዘጠና (90) ቀናት ይሆናል፣ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያሰሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት። እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

English
Hibret Bank S.C. wishes to lease out the 9th floor of its newly constructed Hibir Building, located in Addis Ababa, Ledeta Sub-city, Woreda 7, Sengatera area, for office use through an open competitive bid. Bid No.: Hib/001/2019. Bidders may purchase the bid document starting from Meskerem 9, 2019 E.C. (two days after the first newspaper publication) until Meskerem 21, 2019 E.C. by paying a non-refundable fee of Birr 500.00 (Five Hundred) at nearby Hibret Bank branches to account number IN0403007. The bid document can be obtained from the Procurement and Contract Administration Department, located at the Bank's Head Office Building, 19th floor, Ledeta Sub-city, Woreda 7, Sengatera area. Bidders who wish to visit the floor offered for rent may do so while the bid remains open, i.e., from Meskerem 7, 2019 E.C. to Meskerem 21, 2019 E.C., on Mondays, Wednesdays, and Fridays from 3:00 to 10:00 in the morning at the Bank's Head Office. Before submitting the completed bid document, bidders must carefully review the instructions to bidders included in the bid document. Bidders must submit a bid bond (Bid Bond) equal to one-fourth (25%) of one month's rent they would pay if they lease the offered property, in the form of a bank payment order (CPO) when submitting the bid document; the validity date of the bond shall be ninety (90) days. The bank payment order (CPO) for the bid bond must be issued by any bank other than Hibret Bank. Each bid document must be submitted in a sealed envelope. Bidders must fulfill the necessary documents for the bid and submit them to the Procurement and Contract Administration Department, located at the Bank's Head Office Building, 19th floor, Ledeta Sub-city, Woreda 7, Sengatera area.
ዝርዝሮች · Details
  • 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 25% of one month's rent, in CPO, valid for 90 days, issued by a bank other than Hibret Bank
  • 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 500.00 Birr (non-refundable)
  • 📥 ማስረከቢያ · Submit to: Hibret Bank Head Office Building, 19th floor, Procurement and Contract Administration Department, Ledeta Sub-city, Woreda 7, Sengatera area, Addis Ababa
  • ⏳ የጨረታ ጊዜ · Bid validity: 90 days
አድራሻ · Contact
🏢 Hibret Bank S.C.
📍 Ledeta Sub-city, Woreda 7, Sengatera area, Addis Ababa, Ethiopia

ምንጭ · Source

ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)

🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ

Get tenders like this the moment they publish.

Subscribe →