BinaSmart ዜና 💼 Own a company?
አቅርቦት Supply

የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

Bid Notice for the Purchase of Garment and Leather Sewing Machines

Hand in Hand Holistic Children Service·📍 Ethiopia
🗓 Deadline: 24 Sept 2026

የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት በ'Windows of Hope Project 2026' ስር ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት፡ ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)፣ ብሔራዊ የሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅት (NYWCO)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት (AACDCO)፣ ሪዲም ዘ ጄኔሬሽን (RtG)፣ ፌዝ ኢን አክሽን (FIA)፣ ዱካ የወጣቶች መር ድርጅት (DYLO)፣ አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)፣ ቤተሳይዳ በጎ አድራጎት ድርጅት (BCO) እና ኢንዱራንስ የወጣቶች ማህበር (EYA) በ'Windows of Hope Project 2026' ስር ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፓርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከጷግሜ 2, 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመራው የቴሌግራም ቦት username አድራሻ ማለትም @WoH_bid_portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ መሪ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሃንድ ኢን ሃንድ ቢሮ በአካል መጥተው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሃንድ ሆሊስቲክ ችልድረን ሰርቪስ (HinH) ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

English
A consortium of nine partner organizations: Hand in Hand Holistic Children Service (HinH), National Women's Charitable Organization (NYWCO), Addis Ababa City Development Charitable Organization (AACDCO), Redeem the Generation (RtG), Faith in Action (FIA), Duka Youth Mer Organization (DYLO), I Care for the Nation (ICN), Betesaida Charitable Organization (BCO), and Endurance Youth Association (EYA), under the 'Windows of Hope Project 2026', seeks to purchase garment and leather sewing machines through competitive bidding from qualified suppliers. Therefore, bidders interested in participating in the bid may purchase the bid document starting from the date this notice was published in the Reporter newspaper, from Ginbot 2, 2018 E.C., within 10 consecutive working days, through the Telegram bot username managed by the partner organizations, i.e., @WoH_bid_portalbot, or in person at the Hand in Hand office located at the consortium's lead headquarters, Nifas Silk Lafto Sub-city, Woreda 02, on the road from Jemo Michael to Ayertena, at the Muluwengel Church building, 4th floor, by paying a non-refundable fee of 1000 Birr. Bidders must fill in their bid price on the price submission form attached to the bid document and submit the bid security in the name of Hand in Hand Holistic Children Service (HinH) in a sealed envelope as a bank-certified payment order (CPO).
ዝርዝሮች · Details
  • 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 1000 ብር
  • 📥 ማስረከቢያ · Submit to: በቴሌግራም ቦት @WoH_bid_portalbot ወይም በሃንድ ኢን ሃንድ ቢሮ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና መንገድ፣ የሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 4ተኛ ፎቅ
  • 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-25
አድራሻ · Contact
🏢 Hand in Hand Holistic Children Service

ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)

🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ

Get tenders like this the moment they publish.

Subscribe →