BinaSmart ዜና 💼 Own a company?
አገልግሎት Services

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ ይፈልጋል

Global Bank Ethiopia Seeks Cleaning and Messenger Service Manpower Providers via Open Bid

Global Bank Ethiopia S.C.·📍 Ethiopia
🗓 Deadline: 5 Oct 2026

ስለ ጨረታው · About this tender

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ኃይል አቅርቦት አገልግሎት ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። መመዘኛዎቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል። የጨረታ ቁጥር 05/2026/27። ተጫራቾች ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራና አሰሪን ለማገናኘት የተሰጠ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ራስ አበበ ዳምጠው ጎዳና (ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00 እስከ 11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተቱ ሆነው ማንኛውም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ግልጽ ጨረታው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

English
Global Bank Ethiopia S.C. invites interested bidders to compete in an open bid for the supply of cleaning and messenger service manpower to its various branch offices. Bid No. 05/2026/27. Bidders must have a work permit issued by the Ministry of Labor and Social Affairs to link labor and employers and be able to present evidence, a renewed business license showing current government tax payment, VAT certificate, taxpayer identification number certificate, and tax clearance certificate. Bidders may purchase the bid document by paying a non-refundable fee of 200.00 Birr at South Global Bank S.C. Stadium Branch and presenting the receipt at the bank's head office located on Ras Abebe Damtew Road (Stadium behind Ethiopia Hotel), National Business Center Building, 7th floor, Procurement and Facility Administration Department, from the date of announcement, Monday to Friday from 2:00 to 6:00 in the morning and 7:00 to 11:00 in the afternoon, and Saturday from 2:00 to 6:00 in the morning. Bidders must submit a bid bond of 10,000.00 Birr in the form of a bank payment order CPO or an unconditional bank guarantee letter. The bid price shall remain valid for 90 days from the date of bid opening. Prices submitted by bidders must include VAT and all costs and government taxes paid. The open bid will close on Meskerem 25, 2019 E.C. at 4:00 in the morning and will be opened on the same day at 4:15 in the morning in the presence of bidders or their legal representatives at the bank's head office hall. The bank reserves the right to partially or fully cancel the bid if it finds a better alternative.
ዝርዝሮች · Details
  • 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 10,000.00 Birr
  • 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 200.00 Birr
  • 📥 ማስረከቢያ · Submit to: Global Bank Ethiopia S.C., Head Office, Procurement and Facility Administration Department, National Business Center Building, 7th floor, Ras Abebe Damtew Road (Stadium behind Ethiopia Hotel)
  • 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-10-05
  • ⏳ የጨረታ ጊዜ · Bid validity: 90 days
  • ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: Bidders must have a work permit from the Ministry of Labor and Social Affairs, renewed business license, VAT certificate, taxpayer identification number certificate, and tax clearance certificate.
አድራሻ · Contact
🏢 Global Bank Ethiopia S.C.
📞 0115581204 or 0115318097
📍 Head Office, Procurement and Facility Administration Department, National Business Center Building, 7th floor, Ras Abebe Damtew Road (Stadium behind Ethiopia Hotel)

ምንጭ · Source

ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)

🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ

Get tenders like this the moment they publish.

Subscribe →