የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Ethiopian Tourist Trading Enterprise Invites Bids for Sale of Used Vehicles
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 500 ከፍለው መግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሠነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሃያ ሁለት ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሸጫ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ከነሐሴ 27 ቀን 2018 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡ ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ድርጅታችን የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዘዋወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙት ተሽከርካሪ ብር 100,00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
The Ethiopian Tourist Trading Enterprise invites bids for the sale of its used vehicles in their current condition and location. Bidders must be Ethiopian citizens and present a valid ID or document proving citizenship when purchasing the bid document. The bid document can be obtained from the enterprise's head office at 22 Mazoria, during working hours, upon payment of a non-refundable fee of 500 Birr. Bidders who purchased the document may inspect the vehicles at their location from Nehasie 27 to Nehasie 30, 2018 E.C., including Saturdays, from 3:00 to 10:00 in the morning. If a vehicle has unpaid customs or other taxes, the enterprise will cover them, but transfer, transit, and other costs will be borne by the buyer. Bidders must submit a bid bond of 100,000 Birr per vehicle in the form of a bank-guaranteed CPO, attached to the bid document, before the bid opening.
- 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: ብር 100,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
- 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: ብር 500 (የማይመለስ)
- 📥 ማስረከቢያ · Submit to: የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፣ ሃያ ሁለት ማዞሪያ
- 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-07 10:30
- ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ተጫራቾች
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.