የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች እና መለዋወጫ መሳሪያዎች አቅርቦት ግዥ
Procurement of Electro-Mechanical Items and Spare Parts
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች እና መለዋወጫ መሳሪያዎች አቅርቦት ለመግዛት የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አውጥቷል። ተጫራቾች የተወሰኑ ህጋዊ ሰነዶችን ማሟላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች እና መለዋወጫ መሳሪያዎች አቅርቦት ግዥ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 08/2019 ለመግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርበታል፦ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢ፣ ታክስ ክሊራንስ፣ በግዥ ባለስልጣን የምዝገባ ማስረጃ፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት እና በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት። ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 30 (ሰላሳ) ቀናት ነው። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲሆን በሲ.ፒ.ኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል። ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ ሶፍት ኮፒውን በግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 02/13/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ይሆናል። ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይሆናል። ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
The Ethiopian Toll Roads Enterprise invites eligible bidders for the procurement of electro-mechanical items and spare parts under open national tender No. 08/2019. Any bidder participating in this tender must fulfill the following legal requirements: renewed business license, VAT registration, tax clearance, registration certificate from the Public Procurement Authority, tax payer registration certificate, and a supplier registration certificate in the relevant field. The bid bond amount is 250,000.00 (Two Hundred Fifty Thousand Birr) and must be in the form of CPO or an unconditional bank guarantee. Interested bidders can obtain the soft copy of the tender document from the Procurement Department upon payment of a non-refundable fee of 300 (Three Hundred) Birr at Finance Office No. 01 at the Head Office of the Ethiopian Toll Roads Enterprise. The deadline for bid submission is 02/13/2018 E.C. at 4:00 PM. Bids will be opened on the same day at 4:30 PM. The Enterprise reserves the right to cancel the tender partially or in its entirety.
- 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 250,000.00 ETB (CPO or unconditional bank guarantee)
- 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 300 ETB (non-refundable)
- 📥 ማስረከቢያ · Submit to: የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት (ቱሉ ዲምቱ)
- 📅 መከፈቻ · Opening: 2018-02-13 4:30 PM
- ⏳ የጨረታ ጊዜ · Bid validity: 30 days
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.