የጥበቃ፣ ጽዳትና የአትክልት ልማት አገልግሎት ለማሰራት የጨረታ ማስታወቂያ
Invitation to Tender for Security, Cleaning and Gardening Services
ማህበራችን ለሪል እስቴቱ ግቢ ነዋሪዎች የጋራ ጥቅም አገልግሎቶችን ለማቅረብ ብቃት ያላቸውን የጥበቃ ድርጅቶች አወዳድሮ በዓመታዊ ኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል። ተጫራቾች የሥራውን ዝርዝር እና የጨረታ ቅጽ በ150 ብር ከማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
ማህበራችን ለሪል እስቴቱ ግቢ ነዋሪዎች የጋራ ጥቅም የሚሆን አገልግሎቶችን የሚያቀርብ በመሆኑ ከሚቀርቡ አገልግሎቶች መካከል ለሚከተሉት ሥራዎች ብቃት ያላቸውን የጥበቃ ድርጅቶች አወዳድሮ በዓመታዊ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተፈላጊ አገልግሎቶች፡- በቀን እና በለሊት የጊቢ ሙሉ ጥበቃ፤ በግቢ ውስጥ የጋራ መጠቀሚያ መንገዶችን፣ ቢሮና አካባቢውን እንዲሁም ሌሎች መገልገያ ቦታዎችን ጽዳት መጠበቅ፤ በጊቢው ውስጥ ያሉ የአበባ አትክልትና ሣር ልማት መናፈሻ ቦታዎችን ማልማትና መንከባከብ። ተጫራቾች የሥራውን ዝርዝርና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ከማህበሩ ጽ/ቤት በብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚችሉና ጊቢውንም ተዘዋውረው የሥራውን ዓይነትና መጠን ማየት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለማህበሩ ጽ/ቤት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሶስቱንም የሥራ ዘርፍ በተጓዳኝ ለማካሄድ አለበለዚያም አንዱን ብቻ ወይም ሁለቱን ለማካሄድ መጫረት ይቻላል፡፡ ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፤ ተጨማሪ መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0114-71-73-14 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
Our association, which provides common benefit services to the residents of the real estate compound, wishes to competitively select and contract, on an annual basis, qualified security companies for the following tasks: full security of the compound day and night; maintaining cleanliness of common walkways, offices and surroundings, and other utility areas within the compound; and developing and maintaining flower gardens, grass and park areas within the compound. Bidders can obtain the detailed scope of work and bid documents from the association's office upon payment of 150.00 birr (one hundred fifty birr), and may also tour the compound to inspect the nature and extent of the work. Bids must be submitted in a wax-sealed envelope to the association's office within 5 working days from the date this notice appears in the newspaper. Bidders may bid for all three service areas combined, or for one or two of them separately. The association is not bound to accept the lowest or any bid if a better alternative is found. Further information can be obtained during working hours by calling 0114-71-73-14.
- 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 150.00 ETB
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.