ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን የተረፈ ሬንጅ በርሜል እና የሲሚንቶ ከረጢት በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ
DMC Construction PLC Open Bid for Sale of Leftover Bitumen Barrels and Cement Bags
ስለ ጨረታው · About this tender
ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በፕሮጀክቶቹ ላይ የተረፈ የሬንጅ /Bitumen/ በርሜል እና የሲሚንቶ ከረጢት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር እያሰራቸው በሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችን ማለትም ለአስፋልት ስራ ተጠቅሞ የተረፈ የሬንጅ /Bitumen/ በርሜል እንዲሁም የሲሚንቶ ከረጢት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች አግባብነት ካለው መንግስት አካል ለ2018ዓም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ማሟላት አለባቸው። ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ፡- የሬንጅ /Bitumen/ በርሜል የሚገኘው በአማራ ብሄራዊ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ በድርጅቱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ካምፕ ውስጥ ነው። የሲሚንቶ ከረጢቱ የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ን/ስ/ላ ክፍለ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል የዲ.ኤም.ሲ ሪል እስቴት ጊቢ ውስጥ ነው። ተጫራቾች ሊገዙት ያሰቧቸውን እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ስም በተዘጋጀ P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የገዣቸውን ንብረቶች የትራንስፖርት ወጪ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ ጨምሮ በራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል። ተጫራቾች ያገለገሉ እቃዎቹን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ P.O. ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል አደባባይ ዲ.ኤም.ሲ ሪል እስቴት ህንፃ 10ተኛ ፎቅ ዋና ስራ አሲኪያጅ ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል አደባባይ ዲ.ኤም.ሲ ሪል እስቴት ህንፃ 10ተኛ ፎቅ ዋና ስራ አሲኪያጅ ቢሮ ይከፈታል። አንድ ተጫራች ለሁለቱም ወይም ከሁለት ለአንዱ ንብረት መወዳደር ይችላል።
DMC Construction PLC wishes to sell various construction leftover materials from its ongoing projects, namely leftover bitumen barrels used for asphalt work and cement bags, through an open bid. Organizations interested in participating in the bid must fulfill the requirements of a renewed business license for the year 2018 E.C. from the relevant government body, taxpayer identification number (TIN), evidence of being a VAT payer, and a tax clearance certificate. Location of the assets: The bitumen barrels are located in Amhara National Regional State, West Gojjam Zone, Sekela Woreda, at the company's road project camp. The cement bags are located in Addis Ababa City, Nifas Silk Lafto Sub-city, Lebu Mebrat Hail, inside DMC Real Estate compound. Bidders must deposit a bid bond of 10% of the total price of the items they intend to purchase in the name of DMC Construction PLC via a prepared P.O. Bidders will cover the transportation, loading, and unloading costs of the purchased assets themselves. Bidders can submit the price they are willing to buy the used items for by filling out the prepared price submission form, attaching it with the bid bond P.O., placing it in a sealed envelope, and submitting it to the bid box prepared for the bid at the company's head office located at Nifas Silk Lafto Sub-city, Lebu Mebrat Hail, DMC Real Estate Building, 10th floor, Chief Executive Officer's office, every working day from the date the advertisement is published in the newspaper until September 12, 2019 E.C. at 8:00 AM. The bid will be opened on September 12, 2019 E.C. at 8:30 AM at the company's head office located at Nifas Silk Lafto Sub-city, Lebu Mebrat Hail, DMC Real Estate Building, 10th floor, Chief Executive Officer's office, in the presence of bidders or their legal representatives. One bidder can compete for both or one of the two assets.
- 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 10% of total price of items intended to purchase, in the name of DMC Construction PLC via prepared P.O.
- 📥 ማስረከቢያ · Submit to: DMC Construction PLC Head Office, Nifas Silk Lafto Sub-city, Lebu Mebrat Hail, DMC Real Estate Building, 10th floor, Chief Executive Officer's office, bid box
- 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-22
- ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: Renewed business license for 2018 E.C., TIN number, VAT payer evidence, tax clearance certificate
ምንጭ · Source
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.