BinaSmart ዜና 💼 Own a company?
ሽያጭ ጨረታ Disposal auction

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ - አዋሽ ባንክ አ.ማ

Disposal Auction Notice - Awash Bank S.C.

Awash Bank S.C.·📍 Ethiopia
🗓 Deadline: 8 Oct 2026

ስለ ጨረታው · About this tender

አዋሽ ባንክ አ.ማ በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ200 ብር ገዝተው እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ማስገባት ይችላሉ።

አዋሽ ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ሕንፃና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 በማቅረብ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። የጨረታው መነሻ ዋጋዎች እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራትና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅፅ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል። ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ፤ እንዲሁም ያለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው። የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃለው በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ክፍያውን ፈፅመው ንብረቱን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

English
Awash Bank S.C. wishes to sell the assets listed in the table below through a public auction. To obtain detailed information about the auction, bidders can purchase the bid document for a non-refundable fee of 200.00 Birr (Two Hundred) by depositing it in the name of the bidder at any Awash Bank branch, account number 01540000544500, and presenting the receipt at Awash Bank Balcha Safo Building, 2nd floor, Office of Building and Foreclosed Assets Management, Office No. 1-08, located in Addis Ababa, Lideta, in front of Lideta Church. The bid document can be collected from the date the auction is published in the Reporter Newspaper until Meskerem 27, 2019 E.C. at 11:00 AM. The starting prices and other information are indicated in the bid document. Each bidder must prepare a CPO (Certified Payment Order) for 1/4 (one-fourth) of the starting price of the asset they are bidding for, made in the name of Awash Bank S.C., fill out the form in the bid document, and submit it in a sealed envelope from 2:00 AM to 4:00 AM on Meskerem 28, 2019 E.C. into the box prepared for the auction at Awash Bank Head Office, 12th floor, Procurement and Supply Directorate Office. The auction will be opened on Meskerem 28, 2019 E.C. at 4:15 AM in the presence of bidders or their legal representatives at Awash Bank Head Office, 12th floor, Procurement and Supply Directorate Office. Bid documents submitted after the closing date and time, or without a CPO, will not be accepted. The winners of the auction are obligated to pay Value Added Tax (VAT), name transfer, and related government expenses on the total winning price. The winners must pay the total winning price in full and take delivery of the asset within 15 (fifteen) consecutive working days from the date their winning is communicated by letter. If they fail to pay and take delivery within the specified time, the auction will be cancelled and the deposited money will be forfeited to the bank. The bank reserves the right to cancel the auction in whole or in part if it finds a better alternative.
ዝርዝሮች · Details
  • 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 1/4 (one-fourth) of the starting price of the asset, in the form of CPO (Certified Payment Order) made in the name of Awash Bank S.C.
  • 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 200.00 Birr (non-refundable)
  • 📥 ማስረከቢያ · Submit to: Awash Bank Head Office, 12th floor, Procurement and Supply Directorate Office, auction box
  • 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-10-08
  • ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: Bidders or their legal representatives
አድራሻ · Contact
🏢 Awash Bank S.C.
📍 Awash Bank Balcha Safo Building, 2nd floor, Office No. 1-08, Addis Ababa, Lideta, in front of Lideta Church

ምንጭ · Source

ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)

🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ

Get tenders like this the moment they publish.

Subscribe →