የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዢ ጨረታ
Addis Ababa Abattoirs Enterprise Procurement of Various Items Tender
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ የፅህፈት፣ የቴክኖሎጂ፣ የቧንቧ፣ የኤሌክትሪክ፣ የስራ እና የደንብ ልብስ፣ የፅዳት፣ የብረታ ብረት እና ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2019 መሰረት የተለያዩ እቃዎችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። እቃዎቹም የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የስራ እና የደንብ ልብስ፣ የወንድና የሴት ቆዳ ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ እና ሌሎች መገልገያ እቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ የእርድ መገልገያ እቃዎች፣ የተለያዩ የምርት መገልገያ እቃዎች እና የቱታ ላይ ህትመት የአገልግሎት ግዥ ናቸው። ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ እና TIN የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የታደሰ ክሊራንስ እና በአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 30 ማግኘት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው 2% በሲፒኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነዶች በፖስታ ተዘግተው ከመዝጊያ ሰዓት በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት አለባቸው። ጨረታው መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ይከፈታል። ከተራ ቁጥር 1-5 ያሉት እቃዎች ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት፣ ከተራ ቁጥር 6-9 ያሉት ደግሞ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት በጨረታ ኮሚቴ ይከፈታሉ። ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
The Addis Ababa Abattoirs Enterprise, under tender notice number 3/2019, invites sealed bids for the procurement of various items. The items include various office supplies, technology equipment, pipe fittings, electrical items, work and protective clothing, men's and women's leather shoes, safety shoes and other accessories, various cleaning supplies, various metals, slaughterhouse equipment, production equipment, and printing on hessian cloth services. Bidders must have a valid and renewed business license in the relevant field, VAT registration and TIN certificate, business registration certificate, renewed tax clearance, and proof of supplier registration. Tender documents can be obtained by paying a non-refundable fee of 500 Birr per lot from the Procurement and Property Administration Office, Room No. 30. A bid bond of 2% of the total price must be submitted in the form of CPO, bank guarantee, or cash. Sealed bids must be deposited in the tender box before the closing time. The tender will be opened on Meskerem 19, 2019 E.C. Items 1-5 will close at 4:00 AM and open at 4:30 AM, while items 6-9 will close at 8:00 PM and open at 8:30 PM on the same day. The enterprise reserves the right to cancel the tender in whole or in part.
- 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: 2% of total price in CPO, bank guarantee, or cash
- 📄 የሰነድ ዋጋ · Document price: 500 Birr per lot
- 📥 ማስረከቢያ · Submit to: Tender box at the Addis Ababa Abattoirs Enterprise
- 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-29
- ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: Valid business license, VAT registration, TIN, tax clearance, supplier registration
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.