አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት ንብረቶችን በግልጽ የሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Abyssinia Bank S.C. Invites Public Auction for Sale of Properties under Proclamation No. 97/1990
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ የሐራጅ ጨረታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ የሐራጅ ጨረታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል፡፡ ተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ እዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ወይም ወረዳ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብርና ታክስ ይከፍላል፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች ለመንግሥት የሚከፈለውን የ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ይከፍላሉ፡፡ ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት የሚቻል ሲሆን፣ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 046-212-1710 እና በ046-212-2346 ሀዋሳ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Abyssinia Bank S.C., under the authority granted by Proclamation No. 97/1990 (as amended), invites public auction for the sale of the properties listed in the schedule, in their current condition. Bidders or their legal representatives may participate by depositing 1/4 (one-fourth) of the starting price as a bid bond, via a bank-guaranteed cheque or CPO in the name of Abyssinia Bank S.C. The winning bidder must pay the total price in full within 15 days from the date of notification of award and take possession of the property. If full payment is not made within this period, the auction will be cancelled and the deposited amount will be forfeited to the bank. CPOs of unsuccessful bidders will be returned. The debtor/pledgor may be present at the auction venue on the date and time of the auction; however, if absent, the auction will proceed without them. The winning bidder shall bear all government payments related to the purchased property, as well as any costs related to title transfer. Any outstanding lease payments will be settled by the bank, while remaining lease obligations will be transferred to the winner/buyer. The winning bidder must appear before the city or district administration where the property is located and pay all applicable fees, taxes, and duties. Winners shall also pay 15% VAT, if applicable. Properties may be inspected during working hours by appointment. For further information, call 046-212-1710 or 046-212-2346 in Hawassa. The bank reserves the right to cancel the auction in whole or in part if a better option is found.
- 💰 የጨረታ ማስከበሪያ · Bid bond: ¼ (አንድ አራተኛ) የጨረታ መነሻ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ
- 📅 መከፈቻ · Opening: 2026-09-03 11:00
- ✅ ብቁ ተጫራች · Eligibility: ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው
ምንጭ · Source: Public tender notice (via Reporter Tenders)
🔔 ተመሳሳይ ጨረታዎችን በWhatsApp ይቀበሉ
Get tenders like this the moment they publish.