Ethiopian Federal Police — Cadet Recruitment (2019 E.C.)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 ዓ.ም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ዕጩ ፖሊሶችን እየመለመለ ነው። ዕድሜ 18–25፣ 10ኛ ክፍል እና በላይ። ምዝገባ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም።
The Ethiopian Federal Police is recruiting cadet police officers for the 2019 E.C. budget year across all regional states and the two city administrations, with attention to the fair representation of nations, nationalities and peoples and to gender balance. Successful applicants join the Federal Police Training Centre and, on graduation, are assigned to serve nationwide.
🎓 ስለ ሥልጠናውና ጥቅማ ጥቅሞች
ዕጩ ተመልማዮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ገብተው ሥልጠናውን ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
- በሥልጠና ጊዜ፦ ምግብ፣ መኝታ፣ የሕክምና አገልግሎት፣ አልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።
- ከምረቃ በኋላ፦ በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት ወርሃዊ ደመወዝና የቀለብ ሂሳብ፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በካምፕ የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት አገልግሎትና የሥራ አልባሳት ያገኛሉ።
- በተለያዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች ተወዳድሮ የማደግ ሰፊ ዕድል አለ።
✅ የምልመላ መስፈርቶች
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው/ያላት፤ ለሕገ-መንግሥቱና ለሀገሪቱ ሕጎች ታማኝ የሆነ/የሆነች።
- ከሱሶች የፀዳ/የፀዳች፣ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው/ያላት።
- ዕድሜ ከ18 እስከ 25 ዓመት።
- የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እና በላይ (ላልተካተቱና አነስተኛ ቁጥር ባለባቸው ብሔሮች አካባቢ ቢያንስ 6ኛ ክፍል እና በላይ)።
- ቁመት፦ ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ።
- ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤና ያለው/ያላት (በሕክምና የተረጋገጠ)።
- የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች።
- የወንጀል ሪከርድ የሌለበት/የሌለባት፣ የአሻራ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች።
- ከዚህ በፊት በፖሊስ ወይም በመከላከያ ሠራዊት ሥልጠና ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች።
- ያላገባ/ያላገባች እና ልጅ የሌለው/የሌላት።
- በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን/የምታምን።
- የ7 ዓመት የሥራ ውል ገብቶ በየትኛውም የፌደራል ፖሊስ የሥራ አካባቢ ተመድቦ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች።
📄 በምዝገባ ወቅት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
- የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ 1 ፎቶ ኮፒ።
- ከ2 ዓመት በላይ ነዋሪነትን የሚያሳይ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም የፋይዳ (Fayda) መታወቂያ።
- ከመጨረሻው ትምህርት ቤት፣ ከመኖሪያ ቀበሌ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ-አቀፍ ፖሊስ ጽ/ቤት የተሞላ ፎርም (ከምዝገባ ጣቢያው ይወሰዳል)።
👩 ሴት ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ።
⚠️ ማሳሰቢያ
ማንኛውም ምልምል ከ500 ብር በላይ ገንዘብ፣ ወርቅ፣ ስለታማ ነገሮች፣ ምግብ ነክ ነገሮችና ከሁለት ቅያሪ ልብስ በላይ ይዞ ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መግባት አይፈቀድም።
🗓️ የምዝገባ ጊዜና ቦታ
ምዝገባው ከጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ይካሄዳል። መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በየክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና በምልመላ ጣቢያዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኦፊሴላዊ ማስታወቂያ። BinaSmart ማስታወቂያውን ለአንባቢዎች ምቹ በሆነ መልኩ አቅርቧል — ሙሉ መረጃውን ከኦፊሴላዊው ምንጭ ያረጋግጡ።
🏢 ህንፃ አለዎት?
BinaSmart — ሙሉ የህንፃ አስተዳደር ሲስተም በ24 ሰዓት።