AI for Ethiopian government offices: answering citizens in Amharic, 24 hours a day
ዜጎች ተመሳሳይ ጥያቄ ደጋግመው ይጠይቃሉ፦ ምን ይዤ ልምጣ? ስንት ይከፈላል? የት ነው? AI ረዳት እነዚህን ከተቋሙ ኦፊሴላዊ ሰነድ ላይ ብቻ መልሶ ሠራተኞች ለከባዱ ሥራ ጊዜ እንዲያገኙ ያደርጋል።
በአንድ የመንግሥት ጽሕፈት ቤት በቀን ከሚቀርቡ ጥያቄዎች አብዛኞቹ ሦስት ናቸው፦ ምን ይዤ ልምጣ? ስንት ይከፈላል? የት ነው? 🏛️
እነዚህን መመለስ ዕውቀት አይጠይቅም — ጊዜ ይጠይቃል። ያ ጊዜ ደግሞ ከእውነተኛው ሥራ ይቀነሳል።
መፍትሔው
የተቋሙ ራሱ ሰነዶች — አዋጅ፣ መመሪያ፣ የአገልግሎት ቻርተር፣ የክፍያ ዝርዝር — የሚያነብ ረዳት ይዘጋጃል። ዜጋው በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ ይጠይቃል፤ መልሱም ከተቋሙ ሰነድ ይመጣል።
ለምን ከተራ ቻትቦት ይለያል?
- ከኦፊሴላዊ ሰነድ ብቻ — መልሱ የሚመሠረተው በተሰጠው ሰነድ ላይ ነው። ያልተጻፈውን አይፈጥርም።
- የተሻሩ ሕጎች ይታወቃሉ — ለምሳሌ የግንባታ አዋጅ 624/2009 በ1356/2024፣ የግዥ አዋጅ 649/2009 በ1333/2024 ተተክቷል። ረዳቱ አዲሱን ይጠቅሳል።
- ምን እንደጠፋ ያሳያል — ዜጎች የጠየቁት ግን መልስ ያላገኘው ጥያቄ በዳሽቦርድ ይታያል፤ ይህ የመረጃ ክፍተትዎን ይነግርዎታል።
ተሞክሮ፦ 46 ዘርፍ
ቢናስማርት የኢትዮጵያን የመንግሥት አገልግሎቶች በ46 ዘርፍ ፈትኗል — ፓስፖርት፣ ፋይዳ፣ ግብር፣ ጉምሩክ፣ ፍርድ ቤት፣ መሬት፣ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ግዥ፣ ምርጫ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ሌሎችም። በ138 ጥያቄ ፈተና ውጤቱ ከ58% ወደ 96% አድጓል፤ ዕውቀቱም ከኦፊሴላዊ ምንጮች ብቻ ነው የተወሰደው።
መረጃው የት ይቀመጣል?
የተቋሙ ሰነዶች ተለይተው ይቀመጣሉ፤ ለሌላ ደንበኛ አይታዩም። ሙሉ ሥርዓቱ በተቋሙ ራሱ ሰርቨር ላይ እንዲሆን ከተፈለገ ስለ ግል ተከላ መወያየት ይቻላል።
እንዴት መጀመር ይቻላል?
በአንድ ክፍል ወይም በአንድ አገልግሎት ይጀምሩ — ለምሳሌ "ፓስፖርት" ወይም "የንግድ ፈቃድ"። ሰነዶቹ ይገባሉ፤ ረዳቱ ይሞከራል፤ ከዚያ ይስፋፋል።
ዝርዝሩን በ bina.et/ai-am (አማርኛ) ወይም bina.et/ai (English) ይመልከቱ።
🏢 ህንፃ አለዎት?
BinaSmart — ሙሉ የህንፃ አስተዳደር ሲስተም በ24 ሰዓት።