የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Certificate of Occupational Competence — COC) አንድ ሰው ለሙያው የተቀመጠውን ብሔራዊ የሙያ ደረጃ (Occupational Standard) እንደሚያሟላ በምዘና የሚረጋገጥበት ሰርተፍኬት ነው። ትምህርት ቤት "ተምሬያለሁ" ይላል፤ COC "መሥራት እችላለሁ" ይላል። ምዘናው በፌዴራልና በክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ተቋማት ይሰጣል፤ የመጨረሻው ተቆጣጣሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።
ደረጃ I–II መሠረታዊና ተደጋጋሚ ሥራዎች፤ III–IV ውስብስብ ቴክኒካዊ ሥራና ቁጥጥር፤ V የቴክኖሎጂስት/የአመራር ደረጃ። የቤት ሥራ (domestic work) እና ብዙ የውጭ ሀገር ሙያዎች በዝቅተኛ ደረጃዎች ይመዘናሉ።
የጽሑፍ (ዕውቀት) — ንድፈ ሀሳብ፣ ደህንነት፣ መብትና ግዴታ። የተግባር (አፈጻጸም) — በመዛኝ ፊት እውነተኛ ሥራ፦ ትክክለኛነት፣ ደህንነት፣ የመሣሪያ አጠቃቀም።
ሁለቱንም ያለፈ "ብቁ" (Competent) ተብሎ ሰርተፍኬት ያገኛል። ያላለፈ "ገና ብቁ ያልሆነ" (Not Yet Competent) — ውድቀት አይደለም፤ በዛው ማዕከል በድጋሚ መመዘን ይቻላል።
አዋጅ 1389/2017 አንቀጽ 11 — የምዘና ማዕከሉ ብቃትን ካረጋገጠ ውጤቱን በመረጃ ልውውጥ ሥርዓቱ ያሳውቃል፤ COCዎ ከ Labor IDዎ ጋር ይያያዛል።
In English: the COC certifies that a person meets the national occupational standard for a trade, through a written (knowledge) and a practical (performance) assessment. Levels run I–V. A candidate is rated "Competent" or "Not Yet Competent" and can re-sit. It is issued by federal and regional Occupational Competency Assessment and Certification bodies under the Ministry of Labour and Skills, and since Proclamation 1389/2025 the result is pushed into LMIS against the worker's Labor ID (Art 11).
Who needs it: every overseas worker, whatever the skill category (Arts 12–14, 16); returnees, who now need refresher training plus a COC (Art 16(2)), the opposite of the repealed 1246/2021 rule; TVET graduates; and experience-only workers, whom the centres assess directly (Art 11(2)).
ለውጭ ሀገር ሥራ ያለው መንገድ በአዋጁ (አንቀጽ 10–11) እና በሚኒስቴሩ የአፈጻጸም መመሪያ (ረቂቅ፣ 2018 ዓ.ም፣ አንቀጽ 11–14) እንዲህ ተዘርዝሯል፦
በ lmis.gov.et ተመዝግበው በወረዳ/ቀበሌ አንድ ማዕከል ባዮሜትሪክስ ይስጡ (ሙሉ መመሪያ)። ቅድመ ሁኔታ (መመሪያ አንቀጽ 11)፦ 18 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ ለሥራው ብቃት ያለው፣ በአቅራቢያው ስልጠናና ምዘና ለመውሰድ ፈቃደኛ።
ከተመዘገቡት መስፈርቱን የሚያሟሉት ወደ መንግሥት ቴክኒክና ሙያ ተቋም ወይም ፈቃድ ያለው የግል ማሰልጠኛ ይላካሉ (አዋጅ አንቀጽ 10፣ መመሪያ 11(3))። የማሰልጠኛ ተቋሙ ራሱ በ LMIS የተመዘገበ መሆን አለበት (መመሪያ 12)።
ስልጠና ወር በገባ ከ1–5 ባሉት ቀናት ይጀምራል፤ ያመለጠዎት በሚቀጥለው ወር 1–5 መጀመር ይችላሉ (መመሪያ 13(1)(ለ))። ሚኒስቴሩ የካቲት 2018 እንደገለጸው ወደ ውጭ የተሰማሩ ዜጎች "በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለ21 ቀናት" ሠልጥነዋል፤ በ ILO የተደገፈው የቤት ሥራ ሥርዓተ ስልጠና 30 ቀን ነው። ሲጨርሱ የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ይሰጥዎታል፤ ተቋሙ በ3 ቀናት ውስጥ ለ LMIS ያሳውቃል (13(1)(ሠ)(ሰ))።
የምዘና ማዕከሉ ከማሰልጠኛ የተላከለትን ተመዛኞች በ7 ቀናት ውስጥ ፕሮግራም አውጥቶ በሲስተም ይመዝናል (መመሪያ 14(1))። የጽሑፍ + የተግባር። መታወቂያ (ፋይዳ/ቀበሌ)፣ የስልጠና ማጠናቀቂያ እና ፎቶ ይዘው ይሂዱ።
ብቁ ከሆኑ ሰርተፍኬት ይሰጥዎታል፤ ውጤቱ ለሚኒስቴሩ በሲስተም ይተላለፋል (አዋጅ 11(1)፣ መመሪያ 14(2))። ገና ብቁ ካልሆኑ በዛው ማዕከል በድጋሚ ይመዘናሉ።
ሚኒስቴሩ የሰለጠኑና በምዘና የተረጋገጡ ሠራተኞችን በሥራ ትዕዛዝ ለኤጀንሲዎች ይመድባል (አዋጅ አንቀጽ 7) — ኤጀንሲው አይመርጥም። ከዚያ ሕክምና በተመረጡ ተቋማት (አንቀጽ 17)፣ ውል በ LMIS ይጸድቃል (አንቀጽ 45)።
In English: (1) Labor ID at a one-stop centre — 18+, fit for the job, willing to train nearby (directive Art 11); (2) the Ministry assigns you to a public TVET or licensed private trainer registered in LMIS (Arts 10, 12); (3) training starts on days 1–5 of each month; MoLS cites 21 days, the ILO-supported domestic-work curriculum is 30; completion is reported to LMIS within 3 days (Art 13); (4) the assessment centre schedules you within 7 days, written + practical (Art 14); (5) certificate, result pushed to LMIS, re-sit at the same centre if Not Yet Competent; (6) the Ministry places certified workers with agencies on job orders (Proclamation Art 7), then medical and contract approval.
💬COC ላይ ጥያቄ አለዎት?| ወጪ | ማን ይከፍላል · ምን ይላል |
|---|---|
| የስልጠና ክፍያ | ሠራተኛው (አዋጅ 19(2)(መ))። መጠኑን ሚኒስቴሩ "በጥናት ላይ በመመስረት" ይወስናል (10(4)) — ብሔራዊ አንድ ዋጋ የለም። |
| የ COC ምዘና ክፍያ | ሠራተኛው (19(2)(ሠ))። በክልል ማዕከላት ይለያያል፤ የአማራ ባለሥልጣን የካቲት 2018 "በምዘና ክፍያ ላይ የገበያ ጥናት እየተካሄደ ነው" ብሏል። |
| ስልጠናውን ካላለፉ እንደገና | ከቀድሞው ክፍያ ግማሹን ብቻ (ረቂቅ መመሪያ 13(1)(ረ))። |
| ምዘናውን ካላለፉ እንደገና | በዛው ማዕከል በድጋሚ (14(2))፤ ክፍያው በማዕከሉ ይወሰናል። |
| ሕክምና፣ ቪዛ፣ ትኬት፣ ፈቃድ፣ ኢንሹራንስ | አሠሪው (19(1))። የመጀመሪያው ሕክምና ካልተሳካ ድጋሚው በሠራተኛው (መመሪያ 5(4))። |
| "COC አወጣልሃለሁ" ብሎ ገንዘብ የሚጠይቅ | ሰርተፍኬቱ የሚሰጠው በምዘና ማዕከሉ ብቻ ነው፤ ውጤቱ በሲስተም ነው። ከሠራተኛ ገንዘብ የሚቀበል ኤጀንሲ ፈቃዱን ያጣል (50(4)(i))። |
| ወጪ አውጥተው በአሠሪ/ኤጀንሲ ጥፋት ካልተሰማሩ | ስልጠናና COCን ጨምሮ ይመለስልዎታል (19(4))። |
Who pays: training and the COC are the worker's (Art 19(2)); the Ministry sets training fees by study (Art 10(4)) and assessment fees vary by regional centre, so there is no single national price. Retraining after a failed course costs half the original fee (draft directive Art 13). Employer costs are in Art 19(1); a failed first medical is redone at the worker's cost (directive Art 5). If you paid and were not deployed through the agency's or employer's fault, it is refunded (Art 19(4)).
የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 1389/2017 (1389/2025) — ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 59፣ ነሀሴ 8/2017 (14 August 2025)። አዋጅ 923/2008 እና 1246/2013 ተሽረዋል (አንቀጽ 86)።
የአፈጻጸም መመሪያ (ረቂቅ) — "የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር ----/2018"፣ በአዋጁ አንቀጽ 84(2) መሠረት ሚኒስቴሩ ያዘጋጀው። ⚠️ ቁጥሩና የሚጸናበት ቀን ባዶ ናቸው — ለሕዝብ አስተያየት የወጣ ረቂቅ ነው (ጥቅምት 2018)። የስልጠና መጀመሪያ (1–5)፣ የ3/7 ቀናት ገደቦች እና የግማሽ ክፍያ ደንብ ከዚህ ረቂቅ ናቸው፤ የመጨረሻው መመሪያ ሊለወጥ ይችላል።
ምንጭ፦ የነጋሪት ጋዜጣው የእንግሊዝኛ አምድ፤ የመመሪያው የአማርኛ ጽሑፍ (26 ገጽ)። ደረጃ I–V እና "ብቁ/ገና ብቁ ያልሆነ" አገላለጾች ከቴክኒክና ሙያ ምዘና ሥርዓቱ ናቸው።
ምዘና በክልልና በከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ተቋማት ሥር ባሉ ማዕከላት ይሰጣል። ለውጭ ሀገር ሥራ ማዕከሉን የሚመርጥልዎት ሚኒስቴሩ በ LMIS ነው (የስልጠና ተቋሙ ወደ ማዕከሉ ይልክዎታል)። ለሌላ ዓላማ (የቴክኒክና ሙያ ተመራቂ፣ የግል ተመዛኝ) በክልልዎ ተቋም ይመዘገባሉ — ማመልከቻ፣ የትምህርት ማስረጃ ኮፒ፣ መታወቂያ፣ 2 ፎቶ እና የክፍያ ደረሰኝ ይጠየቃሉ።
| ክልል / ከተማ | ተቋም · ድረ-ገጽ |
|---|---|
| አዲስ አበባ | የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል (ከተማ አስተዳደር) |
| ኦሮሚያ | OOCAA — oocaa.gov.et / ococ.gov.et |
| አማራ | የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ባለሥልጣን (በ6 ወር 88,000+ ተመዛኞች፣ 75 አዲስ ማዕከላት — የካቲት 2018) |
| ማዕከላዊ ኢትዮጵያ | CERSOCAA — cersocaa.gov.et |
| ደቡብ ምዕራብ | southwestcoc.gov.et |
| አፋር · ሐረሪ · ሶማሌ · ሲዳማ | afarcoc.gov.et · hcoc.gov.et · sococ.gov.et · የሲዳማ COC |
Regional bodies run the centres; their sites resolve inside Ethiopia and mostly time out from abroad. Several offer online certificate verification. For overseas work you do not choose the centre: the training institution hands you over through LMIS.
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Certificate of Occupational Competence) — አንድ ሰው ለሙያው የተቀመጠውን ብሔራዊ የሙያ ደረጃ እንደሚያሟላ በጽሑፍና በተግባር ምዘና የሚረጋገጥበት ሰርተፍኬት። በፌዴራልና በክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ተቋማት ይሰጣል።
አዎ። አዋጅ 1389/2017 አንቀጽ 16(1) — ማንኛውም ወደ ውጭ ሀገር ለሥራ የሚሰማራ ሠራተኛ ከሚመለከተው የትምህርት ተቋም ወይም የምዘና ማዕከል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መያዝ አለበት። ያለ COC መላክ የኤጀንሲውን ፈቃድ ለ3 ወር ያሳግዳል (አንቀጽ 50)።
አዎ። አንቀጽ 16(2) — ተመላሽ ሠራተኛ የማደሻ ስልጠና ወስዶ ከምዘና ማዕከል COC ይይዛል፤ ወደ ሌላ የሙያ መስክ ከሆነ አዲስ ስልጠና (16(3))። የቀድሞው ሕግ "ያለ ስልጠና" ይል ነበር — ተሽሯል።
"ገና ብቁ ያልሆነ" (Not Yet Competent) ይባላሉ፤ በዛው ማዕከል በድጋሚ መመዘን ይችላሉ። ስልጠናውን ያላለፉ ከቀድሞው ክፍያ ግማሹን ብቻ ከፍለው እንደገና ይሰለጥናሉ (ረቂቅ መመሪያ አንቀጽ 13)።
ብሔራዊ የተቀመጠ አንድ ዋጋ የለም — የስልጠና ክፍያ በሚኒስቴሩ በጥናት ይወሰናል (አንቀጽ 10(4))፣ የምዘና ክፍያ በክልል ማዕከላት ይለያያል። በአዋጁ አንቀጽ 19(2) መሠረት ስልጠናውንና COCን የሚከፍለው ሠራተኛው ነው።
ሚኒስቴሩ የካቲት 2018 "ለ21 ቀናት" ብሏል፤ በ ILO የተደገፈው የቤት ሥራ ሥርዓተ ስልጠና 30 ቀን፣ የፀጉር ሥራ 40 ቀን ነው። በሙያውና በተቋሙ ይለያያል።
Labor ID · ፓስፖርት · ፋይዳ · ባንክ — ሁሉም መመሪያ በአንድ ቦታ።
🪪 Labor ID መመሪያ → 💬 እገዛ በ WhatsApp